የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው ወደ ትግራይ ክልል ዘልቀው መግባታቸውን እንደተመለከቱ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአዲግራት ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው ወደ ትግራይ ክልል ዘልቀው መግባታቸውን እንደተመለከቱ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአዲግራት ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። የፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒም ነዋሪዎችን ጠቅሶ የኤርትራ ወታደሮች በአዲግራት ከተማ በኩል በስተደቡብ ወደ ማዕከላዊው የትግራይ ክፍል መሰማራታቸውን ዘግቧል። ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኤርትራ ወታደሮች በአዲግራት ከተማ በኩል ወደ ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች በጭነት ተሽከርካሪዎች እና በእግራቸው ሲያቋርጡ የተመለከቱት ከዛሬ ረቡዕ መስከረም 27/ 2019 ዓ. ም. ማለዳ ጀምሮ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የመሰማራታቸው ዜና የተሰማው የትግራይ አስተዳደርን ተቆጣጥሮ የነበረው እና የኢትዮጵያ መንግሥት በኤርትራ ይደገፋል የሚለው የህወሓት ኃይሎች ዋና ከተማዋ መቀለን ለቅቀው…
Read the full story at natnaelmekonnen21 ↗