ኢትዮጵያ ኤርትራን ወራር በመፈጸም የከሰሰች ሲሆን ወታደሮቿ በአስቸኳይ የኢትዮጵያን ምድር ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-10-07 20:45:37 UTC
AdYour ad here[email protected]

ኢትዮጵያ ኤርትራን ወራር በመፈጸም የከሰሰች ሲሆን ወታደሮቿ በአስቸኳይ የኢትዮጵያን ምድር ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች። የኤርትራ ወታደሮች ወደ ሉዓላዊ የኢትዮጵያ ግዛት መግባታቸውን ኢትዮጵያ አሳውቃለች። እነዚህ የኤርትራ ኃይሎች በአስቸኳይ ከሀገሪቱ ግዛት እንዲወጡ አስጠንቅቃለች። ለ ' ብሉምበርግ ' ቃላቸውን የሰጡት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትአለም መለሰ፣ " በሉዓላዊ ግዛታችን ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም የውጭ ኃይሎች በአስቸኳይ ሊወጡ ይገባል " ብለዋል። በተለይም በትግራይ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የኤርትራ ኃይሎች የኢትዮጵያን ግዛት ሳይዘገዩ በፍጥነት ለቀው መውጣት እንዳለባቸው አስጠንቅቀዋል። መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]