ኢትዮጵያ እና እስራኤል ትብብራቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ተስማሙ
ኢትዮጵያ እና እስራኤል ትብብራቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ተስማሙ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ብንያሚን ናታንያሁ ጋር በስልክ ተወያዩ። ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ ግንኙነትና በወቅታዊ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን፣ በጋራ የጥቅም አጀንዳዎች ላይ ያላቸውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል መስማማታቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ውይይቱ ውጤታማና በጎ መንፈስ የተላበሰ እንደነበር ጠቁመዋል። ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፎቶው ፋይል ከዛሬ 5 ዓመት ነው:: #ዳጉ_ጆርናል
Read the full story at zena24now ↗