ህፃናትን ጡጦ አስይዞ ማስተኛት ለጆሮ ኢንፌክሽን ሊያጋልጣቸዉ ይችላል ተባለ

ZENA24NOWneutral2026-10-12 16:24:25 UTC
AdYour ad here[email protected]

ህፃናትን ጡጦ አስይዞ ማስተኛት ለጆሮ ኢንፌክሽን ሊያጋልጣቸዉ ይችላል ተባለ 👉 ይህ ድርጊት ህፃናቱን ለሳንባ ምች እና ለተደጋጋሚ ኢንፌክሽን የመጋለጥ ዕድላቸዉንም ሰፊ ያደርገዋል ነው የተባለው በግንዛቤ ማጣትም ይሁን በተለያዩ ምክኒያቶች ህፃናት እንዳያለቅሱ ተብሎ ጡጦ እየጠቡ እንዲተኙ ማድረግ ለተለያዩ የጤና ችግሮች ተጋላጭ እንደሚያደርጋቸዉ ተጠቁሟል ። በሙራ የዉስጥ ደዌ እና ህፃናት ስፔሻሊስት ክሊኒክ ሜዲካል ዳይሬክተር እንዲሁም የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ዶክተር አብዱልአዚዝ አሊ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ህፃናት ጡጦ ይዘዉ በሚተኙበት ወቅት ወተቱ በጥርሳቸዉ ዉስጥ በመከማቸት አሲድ ይፈጥርና ጥርሳቸዉ እንዲበሰብስ ምክኒያት ይሆናል ። ይህም የወደፊት ዋና ጥርሳቸዉን የአበቃቀል ሂደት ከማበላሸት ባለፈ የአነጋገራቸውን እና የፊት ቅርፃቸዉን ገፅታ ሊያበላሽ እንደሚችል ተመላክቷል…

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]