🤩ወጣት ዮርዳኖስ አምበሉ🤩

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-10-13 19:49:28 UTC
AdYour ad here[email protected]

🤩ወጣት ዮርዳኖስ አምበሉ🤩 የአካውንቲንግ የማዕረግ ተመራቂዋና በስራ ላይ የተሰማራችው ዮርዳኖስ አምበሉ የተባለች ወጣት በአዲስ አበባ ከተማ ወመዘክር እያለች ምሽት ላይ " በስለት ተወግታ " ተገድላለች። ግድያውን በመፈጸም የተጠረጠረው አብሯት ይሰራ የነበረና የፍቅር ጥያቄ አቅርቦ ያልተቀበለችው ግለሰብ ነው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሟቿ ላይ ስለተፈጸመው ትክክለኛ ነገር የቅርብ ቤተሰቦቿን አነጋግረናል። ጠበቃና የሕግ ባለሙያ የሟቿ የቅርብ ቤተሰብ አቶ በርታ በቀለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ? ወጣት ዮርዳኖስ ባለፈው ሳምንት ወመዘክር ግቢ ውስጥ ምሽት ላይ በስለት ተወግታ ሕይወቷ ማለፉን ገልጸዋል። " አስከሬኗን አይቻለሁ። በመጀመሪያ ከጀርባ ሽንጧ ላይ ነው የወጋት፤ ልትከላከል ዞር ስትል ቦርሳዋ ሁሉ ተወግቷል " ሲሉም እማኝነታቸውን ሰጥተውናል። " ስድስት፣ ሰባት ቦታዎች ላይ ነው በስለት…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]