የተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ለነጋዴዎች በርካታ ማቃለያዎችን ይዞ መጥቷል ተባለ
የተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ለነጋዴዎች በርካታ ማቃለያዎችን ይዞ መጥቷል ተባለ የተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1425/2018 የንግዱን ማኅበረሰብ የሚጠቅሙና አሠራርን የሚያቃልሉ በርካታ ለውጦችን ማካተቱን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ የሕግ ተገዢነት ዘርፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ባሳ እንዳስታወቁት፤ አዲሱ አዋጅ ወደ አገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የሚከፈለውን ቀረጥና ታክስ በአንድ ጊዜ መክፈል ለማይችሉ ነጋዴዎች፣ ዕቃዎቻቸውን በክፍልፋይ ማስለቀቅ የሚችሉበትን ዕድል ፈጥሯል። ከዚህ ቀደም ነጋዴዎች በርካታ ኮንቴይነሮችን በአንድ ሰነድ ሲያስመጡ የሁሉንም ዕቃዎች ቀረጥ ሙሉ በሙሉ መክፈል ወይም ተመጣጣኝ ማስያዣ ማቅረብ ይገደዱ እንደነበር ይታወሳል ሲል ኮሚሽኑ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አሳውቋል። በተጨማሪም ነጋዴዎች አስፈላጊውን የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ለማጠናቀቅ የሚያስችላቸው…
Read the full story at addis_news ↗