🚚 የተባበሩት መንግስታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ፦
🚚 የተባበሩት መንግስታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ፦ - አስፈላጊ መድኃኒቶች፣ - የእናቶች እና ሕፃናት የጤና መጠበቂያዎች፣ - አልሚ ምግቦች፣ - የትምህርት ቁሳቁሶች ትግራይ መቐለ ከተማ መግባታቸውንና በግጭቱ ለተጎዱ ቤተሰቦች እንደሚደርስ አሳውቋል። በተመሳሳይ ከጥቂት ቀናት በፊት የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመተባበር 7 የጭነት ተሽከርካሪ ሙሉ ሕይወት አድን የሕክምና ቁሳቁሶችን መቐለ ያደረሰ ሲሆን በክልሉ ለተጎዱ የጤና ተቋማት ውሏል። በሌላ በኩል የቀይ መስቀል ኮሚቴ በአማራ ክልል በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች ለሚገኙ ለላሊበላ እና ሰቆጣ ሆስፒታሎች እንዲሁም ለኩርባ እና ኩልመስክ ጤና ጣቢያዎች አስፈላጊ የሕክምና ግብአቶችን ለግሷል። ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Read the full story at tikvahethiopia ↗