የኤርትራ ጦር በድንበር አካባቢ ምሽግ መቆፈርና ከሕወሃት ኃይሎች ጋር ቅንጅታዊ አሠራር መከተል መጀመሩ ተሰማ።

ADDIS_REPORTERneutral2026-10-16 19:07:26 UTC
AdYour ad here[email protected]

የኤርትራ ጦር በድንበር አካባቢ ምሽግ መቆፈርና ከሕወሃት ኃይሎች ጋር ቅንጅታዊ አሠራር መከተል መጀመሩ ተሰማ። በትግራይ ሰሜን ምዕራብ ዞን አዲ አሠር እስከተባለ ቦታ ድረስ ዘልቆ የገባው የኤርትራ ሠራዊት ጥቅምት 3 ቀን ከአካባቢው በመልቀቅ ድንበር አካባቢ አዲ ጸጸር እና ዲችናማ ወደተባሉ አካባቢዎች ተሠማርቷል ተብሏል። የሕወሃት አርሚ 70 የተወሠኑ ተዋጊዎችም ከኤርትራ ሠራዊት ጋር ተቀላቅለው እየተንቀሳቀሱ መኾኑን ተረድተናል። የኤርትራና የሕወሓት ወታደራዊ አዛዦች፣ ዲችናማ በተባለ አካባቢ በቅርቡ ተሰብስበው፣ ወታደራዊ እቅዶችን ማውጣታቸውና የወታደራዊ መረጃ ልውውጥ ለማድረግ መስማማታቸውንም ምንጮች ገልጸዋል። የኤርትራ ወታደሮች በብዛት ኢሮብ ወረዳ በመግባት፣ የመከላከያ ምሽጎችን በመቆፈር ላይ እንደሚገኙም ሠምተናል። Via:-ዋዜማ @Addis_Reporter @Addis_Reporter

Read the full story at addis_reporter ↗
AdYour ad here[email protected]