#Update
#Update የኢሕአፓ አመራር አቶ አበበ አካሉ በዋስትና ከእስር ተፈቱ። በሽብር ወንጀል ተከሰው እስር ላይ የነበሩት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አመራር አቶ አበበ አካሉ ዛሬ ምሽት ከእስር መፈታታቸውን ተረጋግጧል። አቶ አበበ ምሽት 12:00 ገደማ ላይ ከእስር ከተፈቱ በኋላ ወደ ቤታቸው መግባታቸውን በስልክ ደውለው እንዳሳወቋቸው ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ገልጸዋል። ከእስር የተፈቱት በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተወሰነ እና በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፀና የብር 50,000 ዋስትና መሆኑን ደግሞ የኢሕአፓ ፕሬዚዳንት አቶ አብርሃም ሃይማኖት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል። ፍርድ ቤቱ የዋስትና ውሳኔውን የሰጠው መስከረም 27 ቀን ቢሆንም፣ የዋስትና ገንዘቡ ተይዞም አቶ አበበ እስካሁን ሳይፈቱ መቆየታቸው ጠቅሰዋል። ከአቶ አበበ አካሉ ጋር በእስር ላይ የሚገኙት የፓርቲው…
Read the full story at tikvahethiopia ↗