በትግራይ የሚገኙ አራቱ ዩኒቨርሲቲዎች የመማር-ማስተማር ሒደት ለማስጀመር ያሉበትን ሁኔታ እና የወደፊት አቅጣጫ የገመገመ ውይይት በመቐለ ከተማ መድረክ ተካሒዷል።
በትግራይ የሚገኙ አራቱ ዩኒቨርሲቲዎች የመማር-ማስተማር ሒደት ለማስጀመር ያሉበትን ሁኔታ እና የወደፊት አቅጣጫ የገመገመ ውይይት በመቐለ ከተማ መድረክ ተካሒዷል። መድረኩን የመሩት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የትምህርት ሚኒስትሩ አማካሪ ክንደያ ገብረሕይወት (ፕ/ር)፣ አራቱም ተቋማት (መቐለ፣ ዓዲግራት፣ አክሱም እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች) በትብብርና በቁርጠኝነት በመስራት የትምህርት ሒደቱን ለማስቀጠል እንዲጥሩ አሳስበዋል። በውይይቱ የተሳተፉት የአራቱም ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮች መደበኛ የመማር-ማስተማር ሒደቱን ለማስቀጠል ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል። ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ከሌሎች የፌዴራል ተቋማት ሊደረግላቸው ስለሚገባ ድጋፍም ሀሳቦቻቸውን አቅርበዋል። አራቱም ዩኒቨርሲቲዎች በቀጣይ ሥራዎቻቸው ላይ በተከታታይ እየተናበቡ እንዲሠሩ የሚያስችል የጋራ የትብብር መድረክ…
Read the full story at tikvahuniversity ↗