የፈረንሳይ ከንቲባ ላይ ጥቃት የፈጸሙ እስራኤላውያን ሰፋሪዎችን እንዲታሰሩ ፓሪስ ጥሪ አቀረበች
የፈረንሳይ ከንቲባ ላይ ጥቃት የፈጸሙ እስራኤላውያን ሰፋሪዎችን እንዲታሰሩ ፓሪስ ጥሪ አቀረበች የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዣን ኖኤል ባሮት የእስራኤል መንግሥት በዌስት ባንክ ውስጥ የታይቤህ መንደርን ሲጎበኙ የነበሩ የፈረንሳይ ከንቲባ ላይ ጥቃት የፈጸሙ የእስራኤል ሰፋሪዎችን እንዲያስር ጥሪ አቅርበዋል። የኦልኖዬ-አይሜሪስ ከንቲባ የሆኑት በርናርድ ባውዶክስ “በዌስት ባንክ ውስጥ በአክራሪ ሰፋሪዎች በኃይል ጥቃት እንደተፈጸመባቸው” ባሮት ተናግረዋል። የእስራኤል ባለሥልጣናት “ይህንን የወንጀል ጥቃት በአስቸኳይ ማስቆም እና የሲቪል ህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ አለባቸው” ሲሉ ባሮት በዛሬው ዕለት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በጻፉት ጽሑፍ አክለዋል። በኤፍራታ ሚሊየን #ዳጉ_ጆርናል
Read the full story at zena24now ↗