በህክምና ታሪክ የመጀመሪያው የመነጋገሪያ ክስተት፦ በአይን ምህዋር ውስጥ የበቀለው ያልተጠበቀ ጥርስ
በህክምና ታሪክ የመጀመሪያው የመነጋገሪያ ክስተት፦ በአይን ምህዋር ውስጥ የበቀለው ያልተጠበቀ ጥርስ በህክምናው ዓለም እጅግ ያልተለመደ እና አጃኢብ የሚያስብል አጋጣሚ በህንድ አራቪንድ የአይን ህክምና ሆስፒታል የተመዘገበ ሲሆን፣ የ16 ዓመት ታዳጊ በአይኑ አካባቢ ባጋጠመው እብጠት ምክንያት ወደ ህክምና ተቋም ካመራ በኋላ በምርመራ የተገኘው ውጤት መላውን የህክምና ባለሙያዎች አስገርሟል። ታዳጊው በግራ አይኑ የዐይን ሽፋሽፍት አካባቢ ምንም አይነት ህመም የሌለው እብጠት ተስተውሎበት ወደ ሆስፒታል ያመራ ሲሆን፣ ከአንድ ወር ገደማ በኋላ በዐይን ሽፋሽፍቱ እና በቅንድቡ መካከል ሁለት አነስተኛ፣ ጠንካራ እና ነጭ የሆኑ አካላት ብቅ ብለዋል። ጉዳዩ ያሰጋቸው የህክምና ባለሙያዎች የተከሰተው ነገር ጥርስ ይሁን ወይም አልፎ አልፎ የሚከሰት እጢ ለመለየት የሲቲ ስካን ምርመራ አድርገዋል።…
Read the full story at addis_reporter ↗