በአበርገሌ ከ72 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ይፈልጋሉ።
በአበርገሌ ከ72 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ይፈልጋሉ። በኤልኒኖ ምክንያት በዋግ ኽምራ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ በተከሰተው ድርቅ ከ80 ሺህ 874 ነዋሪዎች ውስጥ ከ72 ሺህ በላይ የሚሆኑት አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እንደሚፈልጉ የወረዳው ግብርና ልማት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ መሠረት ወልደየሱስ እንዳሉት፣ በወረዳው ከሚለማው 17 ሺህ 941 ሄክታር መሬት ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው ሰብል ምርት አልሰጠም። ድርቁ በነዋሪዎችና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የገለጹት ኃላፊዋ፣ 241 አባወራና እማወራዎች፣ በአጠቃላይ 1,531 የቤተሰብ አባላት፣ ቤታቸውን ዘግተው መሰደዳቸውን አስታውቀዋል። በድርቁ ምክንያት የሃይማኖት ተቋማትና ገዳማት እንኳ እየተዘጉ እንደሚገኙም ተገልጿል። በወረዳው የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት መረጃ…
Read the full story at addis_news ↗