🇰🇪
🇰🇪 በጎረቤት ኬንያ ፖል ማኬንዚ የተባሉ ፓስተር " የዓለም መጨረሻ ደርሷል " በማለት የበርካታ ሰዎች ሕይወት እንዲያልፍ አድርገዋል በሚል ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ማኬንዚ እና 29 የሚሆኑ ተከታዮቻቸው የ191 ሰዎችን ሕይወት በማጥፋት ክስ ቀርቦባቸዋል። ከሟቾቹ ውስጥ ከአንዱ በስተቀር ሁሉም ሕፃናት ናቸው። ፓስተሩ ከፈጣሪ ጋር ለመገናኘት እንድትችሉ በሚል ሕፃናቱ ሕይወታቸው እስከሚያልፍ ድረስ እንዲጾሙ ማድረጋቸው ተገልጿል። የዓለም ፍጻሜን የተመለከተው የፓስተሩ አስተምህሮት ዘመናዊ መድኃኒቶችን እንደ "መጥፎ" የሚቆጥር እና ትምሕርትን የሚከለክል ነው። ማኬንዚ እና 29 ተከታዮቻቸው በቀረበባቸው የግድያ ክስ " ጥፋተኛ አይደለንም " ሲሉ ክሱን ውድቅ ያደረጉ ሲሆን " ማንም እንዲሞት አልተገደደም " በማለት ተናግረዋል። የአገሪቱ ባለሥልጣናት እንዳሉት፣ ማኬንዚ ከተለያየ…
Read the full story at tikvahethiopia ↗