በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን የ23 ዓመቷ ወጣት የሴቶች መብት ተሟጋች መሰለች ካሽንቴት መገደል ቁጣ አስነስቷል

ADDIS_NEWSneutral2026-10-20 16:58:02 UTC
AdYour ad here[email protected]

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን የ23 ዓመቷ ወጣት የሴቶች መብት ተሟጋች መሰለች ካሽንቴት መገደል ቁጣ አስነስቷል የንቃት ወጣቶች ማህበር ምክትል ሰብሳቢና የሴቶች ጥቃት ተከላካይ ጸሐፊ ሆና የምትታወቀው ወጣቷ፣ ጾታን መሰረት ባደረገ አሰቃቂ ድርጊት ሕይወቷ አልፏል። ​የግድያው ዋና መንስኤ ወጣቷ የአራት ልጆች አባት ያቀረበውን የሁለተኛ ሚስትነት ጥያቄ በመቃወሟና ቀደም ሲል የፈጸመባትን የጠለፋ ወንጀል ለሕግ በማመልከቷ የተፈጸመ የበቀል እርምጃ መሆኑ ተገልጿል። ጉዳዩ በመደበኛው የሕግ ስርዓት ፋንታ በባህላዊ ሽምግልና እንዲፈታ መደረጉ ቁጣ አስነስቷል። ​ተጠርጣሪው «ካሳ ከፍዬብሻለሁ» በሚል ሰበብ ተከታታይ ዛቻዎችን ሲሰነዘርባት ቆይቶ፣ የምርቃት ስነ-ስርዓቷን ልታከብር ሁለት ቀናት ሲቀሩት በገበያ ቀን በግፍ ገድሏታል። በሰዓቱ እርዳታ ጠይቃ ብትጮህም፣ አካባቢው የነበሩ…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]