" አርሶ አደሮቹ ዘግይቶ የመጣው ዝናብ ሳያመልጣቸው በጋራ በደቦ ለመስራት ሲረባረቡ ነው ጥቃት የተፈጽሞባቸው የተገደሉት " - ነዋሪዎች
" አርሶ አደሮቹ ዘግይቶ የመጣው ዝናብ ሳያመልጣቸው በጋራ በደቦ ለመስራት ሲረባረቡ ነው ጥቃት የተፈጽሞባቸው የተገደሉት " - ነዋሪዎች ትላንትና ሐሙስ ረፋድ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቡርጂና ኮሬ ዞኖች ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ በሚዋሰኑበት ነደሌ እና ሻፉሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አርሶ አደሮች ተገድለዋል። አርሶ አደሮቹ የተገደሉት ከምዕራብ ጉጂ ዞን ሱሮ ባርጉዳ ወረዳ በኩል በመጡ የታጠቁ ሃይሎች መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ፤ የተገደሉት 5 አርሶ አደሮች መሆናቸውን ገልጸዋል። " ከብቶቻቸውን ይዘው በደቦ የእርሻ ስራ ላይ እና ከብት ጥበቃ ላይ እያሉ ነው የታጠቁ ሃይሎች በከፈቱባቸው ድንገተኛ ጥቃት የተገደሉት " ሲሉ ተናግረዋል። አንድ የቡርጂ ዞን ነደሌ ቀበሌ ነዋሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደ ተናገሩት፣ ሟቾቹ ከኮሬ ዞን ሻፉሌ አከባቢ…
Read the full story at tikvahethiopia ↗