" ደመወዝ መክፈል ይጀመራል " - አቶ ረዳኢ ኃለፎም
" ደመወዝ መክፈል ይጀመራል " - አቶ ረዳኢ ኃለፎም የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የሰራተኞች ደመወዝ መክፈል እንደሚጀምር አሳወቀ። በትግራይ ክልል የሚገኙ ሰራተኞች ደመወዝ እየተከፈላቸው እንዳልሆነና በዚህም ከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር ላይ እንደወደቁ በተደጋጋሚ መነገሩ ይታወቃል። ዛሬ መግለጫ የሰጡት በትግራይ ባለአደራ አስተዳደር የፖለቲካ እና ሕዝብ አደረጃጀት ዋና አስፈጻሚ አቶ ረዳኢ ኃለፎም በቅርቡ ደመወዝ መክፈል እንደሚጀመር አሳውቀዋል። " የመንግስታዊ አገልግሎቶች ይጀምራሉ። ሲቪል ሰርቪሱ ወደ ስራ እንዲገባ መመሪያ ተሰጥቷል " ብለዋል። " ለስራ መግባት የሚያስችል ምንድነው ያለው ? ምንድነው የሌለው ? የሚለው ጥናቶች ተካሂደው ተጠናቀዋል አሁን ወደ ስራ እንገባለን " ሲሉ ገልጸዋል። " ሲቪል ሰርቪሱ ወደ ስራ ሲገባ ያልተከፈለ ደመወዝ እንዳለ ይታወቃል እሱ ይጀምራል "…
Read the full story at tikvahethiopia ↗