ከ10ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ኬኒያ ተሰደዋል‼️

AYUZEHABESHANEWSneutral2026-10-24 16:30:59 UTC
AdYour ad here[email protected]

ከ10ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ኬኒያ ተሰደዋል‼️ የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልሎችን በምታዋስነው የሞያሌ ከተማ በተቀሰቀሰው ግጭት ቢያንስ 10,000 ሰላማዊ ሰዎች የኬንያን ድንበር አቋርጠው መሰደዳቸውን ግጭቶችን የሚከታተለው ዓለም አቀፍ ተቋምና ቀይመስቀል አስታወቁ። የድርጅቶቹ ሃላፊዎችን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዛሬ እንደዘገበው በግጭቱ በርካቶች ሞተዋል የመቁሰል አደጋም ደርሶባቸዋል። ከሞቱት ውስጥ አንዲት የ 13 ዓመት ሕጻን እንደምትገኝበት ታውቋል። ዋቆ ገናሌ የተባለ የዓይን እማኝ ለዜና አገልግሎቱ «የሶማሊያ ተዋጊዎች በከተማዋ ከሚገኙ ህንጻዎች ላይ ሆነው ከባድ መሳሪያዎች ሲተኩሶ፤ የኦሮሚያ ኃይሎች ደግሞ አጸፋዊ ምላሽ ሰጥተዋል» ሲሉ ገልጸዋል። ሌላው የዓይን እማኝ ሑሴን ሐልቀኖ በበኩላቸው «በግጭቱ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ሞተዋል፤ ቆስለዋል» ሲሉ ገልጸዋል። የዜና አገልግሎቱ…

Read the full story at ayuzehabeshanews ↗
AdYour ad here[email protected]