ሞያሌ እንዴት ዋለች ?

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-10-24 19:44:18 UTC
AdYour ad here[email protected]

ሞያሌ እንዴት ዋለች ? ‎ በክልል ባንዲራ መሰቀል ጋር በተያያዘ በሞያሌ የተፈጠረው አለመረጋጋት ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን የደፈነ ሲሆን ከተማዋ ዛሬም በከባድ የተኩስ ልውውጥ ውስጥ መዋሏን የአከባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ‎ ‎" ተኩስ ከተጀመረበት ካሳለፍነው ረቡዕ ጀምሮ በሚዲያ መንግስት ጣልቃ ገብቶ አከባቢውን እንዲያረጋጋ ብንጠይቅም ዛሬም ምንም የመጣ ለውጥ የለም " ብለዋል። " ዛሬም በከፍተኛ ተኩስ ውስጥ ነው የዋልነው። አሁንም ቢሆን ላለፉት ሶስትና አራት ቀናት ከቤት ያልወጡ ታማሚዎች አሉ " ብለዋል። " መብራት የተቋረጠበትም አለ። የመጠጥ ውሃ እንደልብ በማይገኝበት ሞያሌ ይህ ሁኔታ ከቀጠለ የበርካቶች ህይወት አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል " ሲሉ በምሬት ተናግረዋል። ቃላቸውን የሰጡን ነዋሪ ትላንት ቱኩሱ በሁዴት ወረዳም እንደነበር ፤ በሞያሌም የሰዎች ህይወት…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]