በእስራኤል የቦምብ ጥቃት በጋዛ የነበሩ 7 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ፡፡

ADDIS_REPORTERneutral2026-10-26 16:52:34 UTC
AdYour ad here[email protected]

በእስራኤል የቦምብ ጥቃት በጋዛ የነበሩ 7 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ፡፡ እስራኤል በጋዛ ከተማ በሚገኝ የዩኒቨርሲቲ ግቢ እና በሌሎች አካባቢዎች በፈፀመችው የአየር እና የከባድ መሳሪያ ጥቃት ቢያንስ ሰባት ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች አስታውቀዋል። እሁድ ዕለት በጋዛ ከተማ በሚገኘው ‘እስላሚክ ዩኒቨርሲቲ’ ላይ በተፈፀመ የአየር ጥቃት ሶስት የደህንነት ጥበቃዎች ተገድለዋል። ይህ ጥቃት ተቋሙን በጥቂት ሰዓታት ልዩነት ውስጥ ኢላማ ያደረገ ሁለተኛው ጥቃት እንደሆነ ተገልጿል። የአልጃዚራ ዘጋቢ ሀኒ ማህሙድ ከስፍራው እንደዘገበው፣ ከጥቃቱ በኋላ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። በግቢው ላይ ከተፈፀመው ሁለተኛ የአየር ጥቃት ጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ በድሮን በተፈፀመ ጥቃት ሰባት ሴት ተማሪዎች የቆሰሉ ሲሆን፣ በደቡባዊ የጋዛ ክፍል በተፈፀመ ሌላ የከባድ መሳሪያ…

Read the full story at addis_reporter ↗
AdYour ad here[email protected]