የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሶማሊያ የነበረውን የፖለቲካ ተልዕኮ ሊያጠናቅቅ ነው
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሶማሊያ የነበረውን የፖለቲካ ተልዕኮ ሊያጠናቅቅ ነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሽግግር እርዳታ ተልዕኮ በሶማሊያ ለሦስት አስርት ዓመታት የቆየውን የፖለቲካ ተልዕኮውን በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም. ሙሉ በሙሉ እንደሚያጠናቅቅ ተገለፀ። ይህ ውሳኔ የተከናወነው የሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግሥት የመንግሥት ግንባታና የአገሪቱን አስተዳደር ኃላፊነት እራሱ ለመረከብ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ነው ተብሏል። የመንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ባሳለፋቸው ውሳኔዎች መሠረት ተልዕኮው ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲከናወን በቆየው የሽግግር ሂደት ኃላፊነቶችን ለሶማሊያ ብሔራዊ ተቋማትና ለተባበሩት መንግሥታት የልማት ኤጀንሲዎች ሲያስረክብ መቆየቱ ተነግሯል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗