«ሌላ የጦር ጀነራል በከበባ ውስጥ ገብተዋል» ተባለ!
«ሌላ የጦር ጀነራል በከበባ ውስጥ ገብተዋል» ተባለ! በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የትግራይ የሰላም ኃይል በጋራ «የመቃረም» ያሉት ዘመቻ እንደቀጠለ ነው። በዛሬው ዕለት በክልሉ የማዕከላዊ ዞን የሚገኙ ከማይቅነጣል እስከ ወርቅአምባ ያሉ መንደሮችነጻ መውጣታቸውን ታውቋል። በናዕዴር አካባቢ የህወሓት ጦር አርሚ 42 አዛዥ የሆኑት ብርጋዴር ጀነራል አብርሃ ተስፋይ በቅፅል ስማቸው «ድንኩል» እና ሌሎች ከፍተኛ አዛዦችም በከበባ ውስጥ መግባታቸውን የሰላም ኃይሉ ባለስልጣን ለዶይቼቬለ ተናግሯል። እስከ አሁን በተካሄዱ ዘመቻዎች በርካታ ከባድና ቀላል የጦር መሳሪያዎች፤ እንዲሆም ወታደራዊ አዛዦች ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውም ተነግሯል።ዶይቼ ቬለ መረጃውን ከነጻ ምንጭ አላረጋገጠም። [DW] @Addis_News @Addis_News
Read the full story at addis_news ↗