አሜሪካ በሚቀጥለው ሳምንት የእስራኤልና ሌባኖስ አዲስ የሰላም ንግግር በዋሽንግተን እንደሚካሄድ አስታወቀች‼️
አሜሪካ በሚቀጥለው ሳምንት የእስራኤልና ሌባኖስ አዲስ የሰላም ንግግር በዋሽንግተን እንደሚካሄድ አስታወቀች‼️ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስራኤልና ሌባኖስ ከሰኔ 16 እስከ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ አዲስ የሰላም ንግግር እንደሚያካሂዱ አስታውቋል። መግለጫው የወጣው እስራኤልና ሄዝቦላህ አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ካወጁ በኋላ ነው። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከሌባኖስ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ አውን ጋር በስልክ በተወያዩበት ወቅት፥ ይህ ድርድር ለሌባኖስ መልሶ ግንባታና ለዘላቂ ሰላም ብቸኛው አማራጭ መሆኑን ገልጸዋል። በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተደረገው የመግባቢያ ሰነድ የሌባኖስን ሉዓላዊነት የሚያከብር ቢሆንም፥ በቅርቡ በእስራኤልና በሄዝቦላህ መካከል የቀጠለውና በደቡባዊ ሌባኖስ የ47 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው ግጭት ስምምነቱን…
Read the full story at esat_tv1 ↗