ፖርቹጋል ኡዝቤኪስታንን 5 ለ ዐ አሸነፈች
ፖርቹጋል ኡዝቤኪስታንን 5 ለ ዐ አሸነፈች አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም ዋንጫ የምድብ 2ኛ ዙር ጨዋታ ፖርቹጋል ኡዝቤኪስታንን 5 ለ ዐ አሸነፈች፡፡ ምሽት 2 ሰዓት ላይ መደረግ በጀመረው ጨዋታ የፖርቹጋልን ግቦች ክርስቲያኖ ሮናልዶ (2)፣ ሜንዴዝ፣ ሊያዮ እና ኔማቶቭ (በራሱ መረብ ላይ) አስቆጥረዋል፡፡ ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ6 የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ጽፏል፡፡
Read the full story at fanatelevision ↗