አንድ የእስራኤል ባለሀብት አዲስ አበባ በሚገኝ ምግብ ቤት ውስጥ ሞተው ተገኙ!!

ADDIS_NEWSneutral2026-10-29 09:52:12 UTC
AdYour ad here[email protected]

አንድ የእስራኤል ባለሀብት አዲስ አበባ በሚገኝ ምግብ ቤት ውስጥ ሞተው ተገኙ!! አንድ የእስራኤል ባለሀብት አዲስ አበባ በሚገኝ አንድ ምግብ ቤት የመጸዳጃ ቤት ውስጥ ረቡዕ ጥቅምት 18 ቀን ሞተው መገኘታቸውን የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የኢትዮጵያ ፖሊስ ከክስተቱ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ የምርመራ ሥራውን ቀጥሏል። በተወሰኑ ዘገባዎች "ራዳ" ተብለው የተጠቀሱት እኚሁ ግለሰብ ለንግድ ሥራ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንደነበርና ወደ መጸዳጃ ቤት ከገቡ በኋላ ለ40 ደቂቃዎች ያህል ሳይመለሱ በመቅረታቸው፣ በቦታው የነበሩ ሰዎች ተከታትለው ሲፈልጓቸው በሽንት ቤት ክፍል ውስጥ ሕይወታቸው አልፎ መገኘቱ ተገልጿል። ምንም እንኳን የሞታቸው መንስኤ እስካሁን በይፋ ባይረጋገጥም፣ ባለሥልጣናት በመርዝ ተመረዘው ሊሆን ይችላል የሚለውን ግምት ጨምሮ ጉዳዩን በመመርመር ላይ…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]