ለወራት ሆርሙዝ ሰርጥ ላይ የቆየችው የኢትዮጵያ መርከብ ጉዞ ጀመረች‼

WASULIFEneutral2026-06-24 12:07:56 UTC
AdYour ad here[email protected]

ለወራት ሆርሙዝ ሰርጥ ላይ የቆየችው የኢትዮጵያ መርከብ ጉዞ ጀመረች‼ ​በኢራንና በአሜሪካ ጦርነት ምክንያት ለወራት ተዘግቶ የነበረው የሆርሙዝ ወሽመጥ በስምምነት መከፈቱን ተከትሎ፣ እዚያው ተዘግቶባት የነበረችው የኢትዮጵያ የጭነት መርከብ "ኤም ቪ ጊቤ" (MV Gibe) ጉዞዋን መጀመሯ ተጠቆመ። ​የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ እንዳስታወቀው፣ መርከቧ በአሁኑ ወቅት በኦማን ገልፍ በኩል ወደ ጅቡቲ በመጓዝ ላይ የምትገኝ ሲሆን፣ ሰኔ 21 ቀን ምሽት 2 ሰዓት ላይ ጅቡቲ ወደብ ትደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል። በወሽመጡ መዘጋት ሳቢያ ከኢትዮጵያ መርከብ በተጨማሪ 1,150 የጭነት መርከቦች ለወራት ለመቆም ተገደው እንደነበር ይታወሳል።

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]