ወደ ሊቢያ ተከለከለ‼
ወደ ሊቢያ ተከለከለ‼ ሊቢያ 📌የኢትዮጵያ ፣ 📌የኤርትራ ፣ 📌 የሶማሊያና 📌ሱዳን ዜጎች ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ ከለከለች። ከፊሉን የሊቢያ ግዛትን የሚቆጣጠሩት በኻሊፋ ሃፍታር የሚመሩት አስተዳዳሪዎች የአራቱን የአፍሪካ ቀንድ አገራት ዜጎች እንዳይገቡ የከለከሉት በሊቢያ የባሕር ዳርቻ በኩል በሕገወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚጓዙ ስደተኞችን ለማስቆም መሆኑ ተነግሯል። በጦርነት የተከፋፈለችው ሊቢያ ከአፍሪካ ቀንድ በተጨማሪ ከሌሎች የአፍሪካ ክፍሎች የተሻለ ሕይወትን ፍለጋ በአደጋኛ ሁኔታ የሚጓዙ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩባት ወሳኝ አገር መሆኗን ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል። #WasuMohammed video 👇Like + Follow👇 https://www.facebook.com/share/18ZGvgBVhp/?mibextid=wwXIfr ==================== To…
Read the full story at wasulife ↗