የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሃካይንድ ሂቺሌማ 24 ሚኒስትሮችን ሾሙ
የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሃካይንድ ሂቺሌማ 24 ሚኒስትሮችን ሾሙ የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሃካይንድ ሂቺሌማ ባለፈው ነሐሴ ወር በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ሁለተኛ የስልጣን ዘመን ማሸነፋቸውን ተከትሎ፣ አዲስ መንግስት ለማቋቋም የሚያስችላቸውን 24 የካቢኔ ሚኒስትሮች ሾመዋል። ፕሬዝዳንቱ በተጨማሪም 10 ግዛታዊ ሚኒስትሮችን ሰይመዋል። ከተሾሙት ባለስልጣናት መካከል ብሬንዳ ታምባታምባ የሀገሪቱ የመጀመሪያዋ የዕድገት እና ማዕድን ሚኒስትር ሆና መሾሟ ተገልጿል። ኤልቪስ ንካንዱ አዲስ የማንነትና ሚዲያ ሚኒስትር እንዲሁም የመንግስት ዋና ቃል አቀባይ ሆኖ ተሾሟል። ፕሬዝዳንት ሂቺሌማ ባቀረቡት ዛምቢያን የማሳደግ አዲስ ማዕቀፍ መሰረት፤ ሀገሪቷ እ.አ.አ በ2031 አዲስ የምርት ግቦችን እንድታሳካ ሚኒስትሮቻቸው ፈጣን እና ተጨባጭ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቅርበዋል። ትግስት ላቀው #ዳጉ_ጆርናል
Read the full story at zena24now ↗