5 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል‼

WASULIFEneutral2026-06-28 20:24:56 UTC
AdYour ad here[email protected]

5 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል‼ በዲላ ከተማ ሚችሌ ክፍለ ከተማ፣ ሀሰደላ ቀበሌ ውስጥ "ዶሮ ሰርቀሻል" በሚል በታጣቂዎች አንዲት ህፃን ሴት ልጅ ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን የዲላ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። ድርጊቱ የተፈጸመው ባለፈው ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ቢሆንም፣ ለፖሊስ የደረሰ ጥቆማ ባለመኖሩ ምክንያት ጉዳዩን ማወቅ የተቻለው ከሁለት ወራት በኋላ (ሰኔ 20 ቀን) በማህበራዊ ሚዲያ ከተሰራጨ ምስል መሆኑን ፖሊስ ገልጿል። በድርጊቱ የተሳተፉ 5 ተጠርጣሪዎች በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር ውለው የወንጀል ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል። ፖሊስ ለተባባሪው ህዝብ ምስጋና አቅርቦ፣ የምርመራውን ውጤት ወደፊት ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል። #WasuMohammed video 👇Like + Follow👇…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]