የሲጋራ ቁራጭ 2 ሺህ ብር ሊያስቀጣ ነው‼
የሲጋራ ቁራጭ 2 ሺህ ብር ሊያስቀጣ ነው‼ በአዲስ አበባ ከተማ የሲጋራ ቁራጭ በመንገድ፣ በአደባባይ ወይም በማንኛውም የሕዝብ መገልገያ ቦታ ላይ የሚጥል ግለሰብ በ2 ሺህ ብር እንደሚቀጣ የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አስታወቀ። ቅጣቱ የሚተገበረው የትምባሆ ምርቶችን አጠቃቀም ለመቆጣጠር በወጣው የከተማ አስተዳደሩ ደንብ ቁጥር 167/2016 መሠረት መሆኑን የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሉእመቤት ታደሰ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በከተማዋ 79 በመቶ የሚሆኑት የሕዝብ መገልገያ ተቋማት ከጭስ ነፃ መሆናቸውንና የአጫሾች መጠን ከ5.3 በመቶ ወደ 4.6 በመቶ መቀነሱን ባለሥልጣኑ አመልክቷል ሲል ብስራት ሬዲዮ ዘግቧል። #WasuMohammed video 👇Like + Follow👇 https://www.facebook.com/share/18ZGvgBVhp/?mibextid=wwXIfr…
Read the full story at wasulife ↗