ደሴ ከተማ በፈነዳ ቦምብ የአንድ ህጻን ህይወት አለፈ፤ ሌላኛው በከባድ ሁኔታ ቆሰለ‼

WASULIFEneutral2026-07-01 08:58:58 UTC
AdYour ad here[email protected]

ደሴ ከተማ በፈነዳ ቦምብ የአንድ ህጻን ህይወት አለፈ፤ ሌላኛው በከባድ ሁኔታ ቆሰለ‼ ​ትናንት ከሰዓት በኋላ 8:00 ሰዓት ገደማ በደሴ ከተማ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ማዶ "ጎረጀርሳ" በተባለ አካባቢ ህጻናት መጫወቻ መስሏቸው የያዙት ቦምብ ፈንድቶ የአንድ የ6 ዓመት ህጻን ህይወት አልፏል። የሟቹ ህጻን ሥነ-ስርዓተ ቀብር ዛሬ የተፈጸመ ሲሆን፣ በቦምብ ፍንዳታው ክፉኛ የቆሰለው ሌላኛው ህጻን ደግሞ በሆስፒታል በጽኑ ታማሚዎች ክፍል ውስጥ ይገኛል። ​የሰሜኑ ጦርነት ትቶት የሄደው ይህ አደገኛ ጠባሳ አሁንም በህጻናት ላይ አደጋ እያደረሰ በመሆኑ፣ ወላጆች እና ቤተሰቦች የልጆቻቸውን ውሎና መጫወቻ ቁሳቁስ በትጋት ሊከታተሉ እንደሚገባ መልዕክት ተላልፏል።ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለሁ። #WasuMohammed video 👇Like + Follow👇…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]