Update

WASULIFEneutral2026-07-01 17:12:48 UTC
AdYour ad here[email protected]

Update "በቃጠሎው 53 መኖሪያ ቤቶችና አንድ መስጂድ ወድመዋል" ወረዳው በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ 023 ቀጅማ ቀበሌ (ቀሰማ ጎጥ) ህፃናት እሳት አያይዘው ሲጫወቱ በተነሳ አደጋ ከ53 በላይ ቤቶች እና አንድ መስጂድ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ወረዳው አስታውቋል። በአደጋው 54 አባወራና እማወራዎችን ያቀፉ 163 የቤተሰብ አባላት ተጎጂ ሆነዋል። የወረዳው ከፍተኛ አመራሮች ጉዳቱን በአካል ተገኝተው የጎበኙ ሲሆን፣ የተጎጂዎችን የጉዳት መጠን በትክክል አጥንቶ በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችል የቴክኒክ ቡድን ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱን ገልፀዋል። የሀብሩ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተስፋዬ ደምሌ ለመንግስት ድጋፍ ጎን ለጎን በጎ አድራጊዎች፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ግብረሰናይ ድርጅቶች ለተጎጂዎቹ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]