" ከ50 በላይ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ተቃጥለዋል። እህል፣ ልብስ ማውጣት አልተቻለም " - መረጃውን ያጣሩ አካልና ተጎጂዎች

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-07-01 18:04:32 UTC
AdYour ad here[email protected]

" ከ50 በላይ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ተቃጥለዋል። እህል፣ ልብስ ማውጣት አልተቻለም " - መረጃውን ያጣሩ አካልና ተጎጂዎች 👉 " ሁለት ህፃናት ከአገዳ ክምር አጠገብ እሳት በማያያዝ ሲጫወቱ በተፈጠረ አደጋ ከ53 ቤቶች በላይ እና አንድ መስጅድ የቃጠሎ አደጋ ደርሶባቸዋል " - ሀብሩ ወረዳ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ከ50 በላይ የአርሶ አደር መኖሪያ ቤቶች ትናንት በእሳት መቃጠላቸውን አንድ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን በተመለከተ የሚሰሩ የአካባቢው ተወላጅ እና ሁለት ተጎጂዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። የዞኑ አደጋ ስጋት ኮሚሽን ጽሕፈት ቤት በበኩሉ የቃጠሎ አደጋው መድረሱን፣ " ከ50 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል " የሚል መረጃ መሰማቱንና ወደ ቦታው ጉዳዩን የሚያጣራ ቡድን ተዋቅሮ መሄዱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። ወንድሙ ከቀናት በፊት የሞተበት ሀዘን ላይ…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]