ቤልጂየም ሴኔጋልን በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቀለች
ቤልጂየም ሴኔጋልን በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቀለች አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም ዋንጫ የ32ቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ቤልጂየም ሴኔጋልን 3 ለ 2 በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቅላለች። ምሽት 5 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ሴኔጋል በሀቢብ ዲያራ እና ኢስማኤላ ሳር ግቦች 2 ለ 0 ስትመራ ብትቆይም፤ በ86ኛው እና በ 89ኛው ደቂቃ ሮሜሉ ሉካኩ እና ዩሪ ቲሊሞንስ ባስቆጠሯቸው ግቦች ቤልጂየም የመደበኛውን ሰዓት ጨዋታ በአቻ ውጤት አጠናቅቃለች። በዚህም ጨዋታው ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አምርቶ ዩሪ ቲሊሞንስ እራሱ ላይ በተሰራ ጥፋት የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት ወደ ግብነት በመቀየር ቤልጂየም 3 ለ 2 እንድታሸንፍ አድርጓል።
Read the full story at fanatelevision ↗