የዓለም የነዳጅ ዋጋ ቀነሰ‼

WASULIFEneutral2026-07-02 09:56:04 UTC
AdYour ad here[email protected]

የዓለም የነዳጅ ዋጋ ቀነሰ‼ ​አሜሪካና ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ዙሪያ በዶሃ ያደረጉት ውይይት አዎንታዊ መሻሻል ማሳየቱን ተከትሎ፣ የአቅርቦት መቋረጥ ስጋት በመቀነሱ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ቅናሽ አሳይቷል። ​በዚህም መሠረት የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በ0.92 በመቶ ቀንሶ በባሬል 70.91 ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዲየት (WTI) ደግሞ በ0.86 በመቶ ቅናሽ በባሬል 67.99 ዶላር ሆኗል። ይህም ካለፈው የካቲት ወር ወዲህ የታየው ዝቅተኛው የዋጋ ደረጃ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። ​የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውይይቱ መሻሻል ማሳየቱን ቢገልጽም፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር የሚያስችል ፍንጭ እስካሁን አልታየም። የሁለቱ ሀገራት ቀጣይ ስብሰባ ከሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. በኋላ እንደሚካሄድ ታውቋል።…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]