በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ በደረሰ ጥቃት የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ‼
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ በደረሰ ጥቃት የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ‼ በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ አገምሳ ከተማና በዙሪያዋ ባሉ መንደሮች ሰኔ 23 ቀን ከለሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ አስተዳደርና ነዋሪዎች ለቢበሲ ገልፀዋል። በጥቃቱ 11 ሰዎች ሲገደሉ 17 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ታውቋል። ከተገደሉት መካከል ሁለቱ ሲቪሎች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ የሚሊሻ አባላት መሆናቸው ተገልጿል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ጥቃቱ የተፈጸመው የአገር መከላከያ ሠራዊት ከአካባቢው በድንገት መውጣቱን ተከትሎ ነው። በጥቃቱም ወቅት መንደሮች የተዘረፉ ሲሆን፣ ወደ 400 የሚጠጉ ከብቶች፣ በጎችና ፍየሎች ተዘርፈው መወሰዳቸውን ነዋሪዎቹ አክለው ገልጸዋል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መረሳ ሳፊታ ጥቃቱ መፈጸሙን አረጋግጠው፣ የክልሉ ጸጥታ ኃይልና…
Read the full story at wasulife ↗