አሳዛኝ አደጋ‼

WASULIFEneutral2026-07-04 16:29:24 UTC
AdYour ad here[email protected]

አሳዛኝ አደጋ‼ ​ዛሬ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. በአማራ ክልል አዊ ዞን ቅዳማጃ መስመር ላይ፣ አንድ ባጃጅ ከሲኖ ትራክ መኪና ጋር በመጋጨቱ የ8 ሰዎች ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ አልፏል። ባጃጁ ከተፈቀደው አቅም በላይ ጭኖ በመጓዙ የተጎጂዎች ቁጥር ሊበራከት እንደቻለ የተገለጸ ሲሆን፣ በትራፊክ ቁጥጥር አካላት ላይም የክትትል መላላት ቅሬታ አስነስቷል። ​በተመሳሳይ ዕለት በጋምቤላ ከተማ አንድ ተሽከርካሪ ሰው ገጭቶ ሕይወት ማጥፋቱን ተከትሎ፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የሟች ዘመዶች ተሽከርካሪውን በጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ፊት ለፊት አቃጥለውታል። የጸጥታ አካላት በቅርበት እያሉ ድርጊቱን አለማስቆማቸው ተጠያቂነት የሚያስከትል ጥፋት መሆኑ የተነገረ ሲሆን፣ አሽከርካሪዎች በከተማ ውስጥ የፍጥነት ወሰንን እንዲያከብሩ የሾፌሮች አንደበት ጥሪ አቅርቧል። ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለሁ።…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]