ተወዳጇ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
ተወዳጇ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች በበርካታ የባህል ሙዚቃ ዜማዎቿ ከፍተኛ አድናቆትን ያገኘችው ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። ድምፃዊቷ ያጋጠማትን የጤና እክል ተከትሎ በሕክምና ስትረዳ ቆይታለች። ራሔል ዮሐንስ በግሏ እናከተለያዩ ድምፃውያን ጋር በመሆን በርካታ ተወዳጅነት ያገኙ ሙዚቃዎችን ሠርታለች። በሙዚቃዎቿ ከድምፃዊነቷ ባለፈ፣ በአንዳንዶቹ ላይ በግጥም እና በዜማ ድርሰትም አስተዋፅኦ ታደርግ ነበር። ራሔል ዮሐንስ ከሠራቻቸው ሙዚቃዎቿ መካከል እንደ "ኢትዮጵያ"፣ "አራዳ"፣ "እንደ ኢየሩሳሌም"፣ "ትዝታ"፣ "አንቺ ባለድሪ"እና "አየር ኃይላችን" የመሳሰሉት ተወዳጅነት አግኝተውላታል። #ዳጉ_ጆርናል
Read the full story at zena24now ↗