" በድርጊታችን ተጸጽተናል" የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች
" በድርጊታችን ተጸጽተናል" የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቀጣና የሰላም አማራጭን ከተቀበሉ ታጣቂዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል። የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ መኮነን አጥናፉ መንግሥት ሁለንተናዊ ሰላምን ለማስፈን ከኅብረተሰቡ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ስለ ሰላም እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል። በዚህም በወረዳው በተለያዩ አካባቢዎች በጫካ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ እየገቡ መኾናቸውን ተናግረዋል። የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎችን በተለያዩ የሥራ እድሎች በዘላቂነት ለማቋቋም እንደሚሠራ አንስተዋል። የሰላምን አማራጭ ያልመረጡ ሌሎች የታጠቁ ኃይሎችም ለሀገር እና ለሕዝብ ሰላም ሲሉ የሰላም ጥሪውን እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል። የቆቦ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ኀይለዓብ ወንድሙ ነፍጥ አንግቦ ጫካ መውጣት ምንም ለውጥ የማያመጣ መኾኑን…
Read the full story at amharamassmedia ↗