5ኛ ዙር ❤️
5ኛ ዙር ❤️ ነዋሪነታቸው በአሜሪካ፣ አትላንታ የሆኑት ድንቅ ባለሙያዎች ዶክተር ተስፋዬ ተሊላ እና ዶክተር ኦብሲኔት መርዕድ ከሀገር ቢርቁም የልባቸው ትርታ ግን ሁሌም ከኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው ጋር ነበር። ይህንን ፍቅር በተግባር ለመግለፅ " Heart Attack Ethiopia " የተባለ ተቋም በመመስረት ባለፉት 4 ተከታታይ ዙሮች ለበርካታ ወገኖቻችን ነጻና እጅግ ከፍተኛ የልብ ህክምና እርዳታ በመስጠት የብዙዎችን ህይወት ታድገዋል ፤ በቤተሰብ ውስጥም ደስታን መልሰዋል። አሁን ደግሞ ለ5ኛ ጊዜ ታላቅ የሆነ የህክምና ዘመቻ ለማድረግ 55 የጤና ባለሙያዎችን ያካተተ ቡድን በመያዝ አዲስ አበባ ገብተዋል። ቡድኑ በተስፋና በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩ 200 ወገኖቻችን ሙሉ በሙሉ ነጻ የልብ ህክምና እርዳታ ይሰጣል። እውቀታቸውን ፣ ጊዜያቸውን ፣ ጉልበታቸውን ፣ ሀብታቸውን ይዘው የሰውን ህይወት…
Read the full story at tikvahethiopia ↗