ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ !

ETHIO_MEREJA_NEWSneutral2026-07-06 08:52:05 UTC
AdYour ad here[email protected]

ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ! በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 የትምህርት ዘመን 97.48% የሚሆኑ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች 50% እና በላይ በማስመዝገብ ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መዘዋወራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አሳወቀ። የ2018 የትምህርት ዓመት የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። ዘንድሮ ፈተናውን ከወሰዱ 84,257 ተማሪዎች መካከል 82,137 የሚሆኑ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ሆኖ የተቆረጠውን 50 በመቶ እና በላይ አስመዝግበዋል። 768 ትምህርት ቤቶች ፈተና አስፈትነው 543 ያህሉ ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ማሳለፋቸው ተገልጿል። ተፈታኝ ተማሪዎች ይህን ሊንክ https://aa6.ministry.et/#/result በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

Read the full story at ethio_mereja_news ↗
AdYour ad here[email protected]