የአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። 📌 የሕክምና ትምህርትን በአፍሪካ ማስፋፋት እና የአህጉሪቱ የጤና ባለሙያዎች ትምህርት ላይ የሚያተኩረው የሕክምና ትምህርት (MedEd Africa 2026) አህጉራዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ከአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ቤቶች ጥምረት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ 2ኛው የ(MedEd Africa) ጉባኤ "የአፍሪካን የጤና ግብረ ኃይል ላልተረጋገጠ መጻኢ ጊዜ ማዘጋጀት፣ አጋርነትን፣ ቴክኖሎጂን፣ ፈጠራን እና አመራርን መጠቀም" በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው። 🎯 የጉባኤው ዋና ዋና ትኩረቶች እና ዓላማዎች፦ ጥራት እና ትብብር፦ በአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ጥራትን ማሳደግ፣ አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከር እና ብቁ የሕክምና ባለሙያዎችን ማፍራት። 👉 የራስን ዕድል በራስ መወሰን፦…
Read the full story at amharamassmedia ↗