የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

AMHARAMASSMEDIAneutral2026-07-06 11:40:49 UTC
AdYour ad here[email protected]

የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ። የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በመደበኛ እና በተከታታይ ትምህርት በመምህርነት ሙያ ያሠለጠናቸውን 818 ተማሪዎች ለ14ኛ ጊዜ አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል 332 የሚኾኑት ኮሌጁ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐ ግብር ያሠለጠናቸው ናቸው። ቀሪዎቹ በዲፕሎማ መርሐ ግብር ሥልጠናቸውን የተከታተሉ ናቸው ተብሏል። በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ እና የኮሌጁ ሥራ አመራር ቦርድ ሠብሣቢ ቴዎድሮስ እንዳለው የመመረቅ ምሉዕነት የሚረጋገጠው ለማኅበረሰቡ በሚሰጠው ጥራት ባለው አገልግሎት መኾኑን ተናግረዋል። ተመራቂዎች ትውልድን በዕውቀት የማነጽ፣ አመለካከቱን የማቃናት እና ገንቢ ትውልድ የመፍጠር ታሪካዊ ኀላፊነት እንዳለባቸውም…

Read the full story at amharamassmedia ↗
AdYour ad here[email protected]