❤️🙏
❤️🙏 ከአሜሪካ በመጡት በዶ/ር ተስፋዬ ተሊላ እና ዶ/ር ኦብሲኔት መርዕድ የሚመራው የ « Heart Attack Ethiopia » የህክምና ቡድን ከአሜሪካው ታዋቂ የ « Mayo Clinic » የልብ ቀዶ ህክምና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር 5ኛውን የልብ ህክምና ዘመቻ በዛሬው ዕለት በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል (TASH) በስኬት ጀምሯል። በመጀመሪያ ቀን ውሎ በከፍተኛ የልብ ህመም ትሰቃይ ለነበረች የ27 ዓመት ወጣት ስኬታማ ክፍት የልብ ቀዶ ህክምና ተደርጎላታል። የህክምና ቡድኑ ለተደረገላቸው መልካም አቀባበልና ለሀገር ውስጥ የጤና ባለሙያዎች ድጋፍ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ❤️ Heart Attack Ethiopia ❤️ @tikvahethiopia
Read the full story at tikvahethiopia ↗