መረጃ‼️

ADDIS_NEWSneutral2026-07-08 10:26:01 UTC
AdYour ad here[email protected]

መረጃ‼️ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት፣ በኤርትራ የተመድ የሰብዓዊ መብት ተቆጣጣሪ ልዩ ራፖርተርን የጊዜ ቆይታ በ23 የድጋፍ ድምጽ በድጋሚ ላንድ ዓመት አራዘመ። የምክር ቤቱ አባል የኾነችው ኢትዮጵያ፣ የልዩ ራፖርተሩን የጊዜ ቆይታ ለማራዘም የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ ደግፋ ድምጽ ሠጥታለች። ኬንያንና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ 17 አገራት ድምጸ ተዓቅቦ ሲያደርጉ፣ ግብጽ፣ ቻይና፣ ቡሩንዲ፣ ፓኪስታን እና ሕንድ የውሳኔ ሀሳቡን ተቃውመዋል። ረቂቅ የውሳኔ ሀሳቡን ያቀረቡት የአውሮፓ አገራት ነበሩ። ኤርትራ፣ ከእንግዲህ በልዩ ራፖርተሩ ዙሪያ ከአጋር አገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደማታደርግ በቅርቡ ማሳወቋ አይዘነጋም። @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]