በሮቤ ከተማ የጤና ባለሙያዉን በደቦ በመደብደብ የአካል ጉዳት ያደረሱ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ
በሮቤ ከተማ የጤና ባለሙያዉን በደቦ በመደብደብ የአካል ጉዳት ያደረሱ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ በሮቤ ከተማ አስተዳደር አዶሼ ክፍለ ከተማ ሮቤ የተሽከርካሪ መናሕርያ ውስጥ አንድን የጤና ባለሞያ በደቦ የደበደቡ ወጣቶች በእስራት ተቀጡ።እንደ ሮቤ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምርያ የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሐላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ጌታቸው ታምሩ ገለፃ 1ኛ ሱልጣን ሑሴን ፣ 2ኛ ኢብራሔም ሑሴን እና 3ኛ ቦንሣ አወሉ የተባሉ ተከሳሾች የአንደኛ ተከሣሽ የእጅ ስልክ ጠፋ በሚል ሠበብ በአንድ የጤና ባለሞያ ላይ በደቦ ከፍተኛ ድብደባ በማድረስ የአካል ጉዳት አድርሰዋል። ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ዓም ከጥዋቱ አንድ ሠዓት ተኩል ላይ አሮጌው መናሕርያ ውስጥ የጊኒር ከተማ ጤና ፅህፈት ቤት የጤና ባለሞያ የሆኑትን ዋቆ ከድር የተባሉትን የአንደኛ ተከሣሽ ሞባይል በመጥፋቱ ወስደኃል በሚል ያልተረጋገጠ…
Read the full story at zena24now ↗