በ20 ቀናት ለቃችሁ እንድትወጡ ተባለ‼️
በ20 ቀናት ለቃችሁ እንድትወጡ ተባለ‼️ በመርካቶ ከ200 በላይ ነጋዴዎች በ20 ቀናት ውስጥ ሱቆቻቸውን እንዲያስረክቡ መታዘዛቸው ተሰምቷል። በአዲስ አበባ መርካቶ ጣና የገበያ ማዕከል ፊት ለፊት የሚገኙ ከ200 በላይ ነጋዴዎች፣ በልማት ምክንያት በ20 ቀናት ውስጥ የንግድ ቤቶቻቸውን ጠቅልለው እንዲያስረክቡ ከፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጥብቅ ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው ተናግረዋል። ነጋዴዎቹ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ቤቶቹን በማያስረክቡ አካላት ላይ ለሚደርሰው የንብረት ጉዳት ኮርፖሬሽኑ ኃላፊነት እንደማይወስድ በደብዳቤው እንደገለፀላቸው ጠቁመዋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗