በሶማሌ ክልል የታሸገ የግመል ወተት ለገበያ እየቀረበ መሆኑ ተገለጸ
በሶማሌ ክልል የታሸገ የግመል ወተት ለገበያ እየቀረበ መሆኑ ተገለጸ በሶማሌ ክልል የታሸገ የግመል ወተት ለገበያ እየቀረበ እንደሚገኝ ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ሚኒስቴሩ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት የግመል ወተት ማሻሻያ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ቴክኖሎጂው አስቸጋሪ በመሆኑ ግመል የማዳቀል ሥራ እየተሠራ ባይሆንም፣ የግመል ወተትን ማሻሻል ላይ ግን ምርቱ በሚገኝባቸው አካባቢዎች በስፋት የተጀመሩ ሥራዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል። የግመል ወተት ምርትን ለማሻሻል እና በአያያዝና በመመገብ በኩል ያለውን ክፍተት በመሙላት ምርቱ እንዲጨምር እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ከአርብቶ አደሩ ምርቱን በመሰብሰብ በሶማሌ ክልል አካባቢ የታሸገ የግመል ወተት ለተጠቃሚው እንዲቀርብ እየተደረገ…
Read the full story at addis_reporter ↗