የቀድሞዉ የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻሜኒ ተቀበሩ።
የቀድሞዉ የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻሜኒ ተቀበሩ። አሜሪካ እና እስራኤል ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ ላይ የገደሏቸዉ የኢራን የፖለቲካና የኃይማኖት መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻሜኒ ዛሬ ተቀበሩ። እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ ጦርነት በከፈቱበት ዕለት የካቲት 28 ቀን 2026 ከኻሜኒ ሌላ ሴት ልጃቸዉን፣ የልጅ ልጃቸውን ፣ አማቻቸውንና 11 ባለሥልጣኖቻቸውን ገድለዋል። ባለቤታቸውም ክፉኛ ቆስለዉ ኋላ ሞተዋል። የኻሜኒ ሥልጣን የያዙት ያሁኑ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ የዚያን ቀን ቆስለዋል። ሞጅታባሕ ጠቅላይ መሪነቱን ሥልጣን ቢይዙም እስከ ዛሬ ድረስ ለሕዝብ እይታ አልቀረቡም። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለአባታቸው በተደረገው የሽኝት ሥርዓትም ሆነ በዛሬው የቀብር ሥርዓት ላይ አልተገኙም። ኢራንን ከ30 ዓመታት በላይ የመሩት ዓሊ ኻሜኒ ዛሬ የተቀበሩት በሐገሪቱ ሰሜን-ምሥራቅ ቅዱስ…
Read the full story at tikvahethiopia ↗