በአከራዮች ላይ ጠንካራ ቅጣት ተደነገገ‼
በአከራዮች ላይ ጠንካራ ቅጣት ተደነገገ‼ በአዲስ አበባ ከተማ የቤት ኪራይ ውል ያላደሱ እና የተቀመጠውን የዋጋ ጣሪያ ያላከበሩ አከራዮች ላይ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣል ተደነገገ። 📌የቤት ኪራይ ውል ሳያድሱ እስከ ሁለት ወር የቆዩ አከራዮች የአንድ ወር ሙሉ ኪራይ እንዲቀጡ ይደረጋል። 📌ከሦስት ወር በላይ ውሉን ሳያድሱ የቆዩ ደግሞ የሁለት ወር የኪራይ ክፍያ ያህል ቅጣት ይጠብቃቸዋል። በተጨማሪም አዲስ ተከራይ አጋብተው ያላስመዘገቡ አከራዮች የአንድ ወር ኪራይ የሚቀጡ ሲሆን፣ 📌 ድርጊቱ በጥቆማ ወይም በክትትል ከተደረሰበት ግን ቅጣቱ እስከ ሦስት ወር የኪራይ ዋጋ ሊደርስ እንደሚችል ተገልጿል። የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሕጉ አከራዮች ውል የማደስና የማሳወቅ ግዴታ እንዳለባቸው በግልጽ ይደነግጋል ብሏል። #WasuMohammed video 👇Like + Follow👇…
Read the full story at wasulife ↗